🔇Unmute
ሚዛን አማን፤ ሐምሌ 3/2018(ኢዜአ)፦ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል 348 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መቅረቡን የክልሉ ማዕድን እና ኢነርጂ ኤጀንሲ አስታወቀ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሰሞኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በወርቅ ምርት እመርታዊ ውጤት መመዝገቡን መግለጻቸው ይታወሳል።
በዚህም በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከወርቅ ማዕድን ምርት 5 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማገኘት የሚያስችል አቅም መፈጠሩን ጠቅሰው፣ ኢትዮጵያ በብዝሀ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ለማዕድን ዘርፍ የሰጠችው ትኩረት ውጤቱን ከፍ ማድረጉንም ተናግረዋል።
የወርቅ ማዕድን ከሚመረትባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች አንዱ በሆነው ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልልም ለዘርፉ በተሰጠ ትኩረት የወቅር ምርት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መጥቷል።

ኢዜአ ያነጋገራቸው የክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው ወልያብ (ዶ/ር) እንዳሉት፣ በክልሉ በበጀት ዓመቱ የተመዘገበው የወርቅ አቅርቦት ምጣኔ ከፍተኛ ነው።
ለእዚህም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 350 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ለማቅረብ ታቅዶ 348 ኪሎ ግራም ምርት መቅረቡን በማሳያነት ተናግረዋል።
አፈጻጸሙ በ2017 በጀት ዓመት ከክልሉ ከቀረበው 155 ነጥብ 5 ኪሎ ግራም የወርቅ ምርት አንጻር ሲታይ በከፍተኛ መጠን ጭማሪ ማሳየቱንም ገልጸዋል።
የለውጡ መንግስት ለማዕድን ዘርፍ በሰጠው ትኩረትና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ባደረጉት ጠንካራ ክተትል የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉንም ጠቁመዋል።
በ2019 በጀት ዓመትም ከዘንድሮ ከፍ ያለ የወርቅ መጠን ለብሔራዊ ባንክ በማቅረብ ሀገራዊ የውጭ ምንዛሬ አቅምን በማጠናከር በኩል ክልሉ ያለውን ሚና እንዲያሳድግ ቅንጅታዊ አሰራር ይጠናከራል ብለዋል።
ለዚህም ተደራጅተው ፈቃድ ያገኙ ወርቅ አምራች ማኅበራት በመሉ አቅም ወደ ተግባር እንዲገቡ በማድረግና አዳዲስ ማኅበራትን በማሰማራት የዘርፉን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማስቀጠል ይሰራል ነው ያሉት።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026