🔇Unmute
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 5 /2018 (ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ በአምስት ዓመታት ውስጥ ከ1 ነጥብ 3 ትሪሊዮን ብር በላይ የካፒታል ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በዓድዋ ድል መታሰቢያ የምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጉባኤው ላይ የከተማ አስተዳደሩን የ2018 በጀት ዓመት ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እያቀረቡ ነው።
ከንቲባዋ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ባቀረቡት የሪፖርት ማብራሪያ፤ ባለፉት አምስት ዓመታት የአዲስ አበባን የኢንቨስትመንት አማራጮች በማስተዋወቅና በማስፋፋት ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።
በዚህም ለ22,190 አልሚ ባለሀብቶች አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ በመስጠት፣ ለ1,632 ነባር ባለሀብቶች ደግሞ የማስፋፊያ ፈቃድ መስጠት መቻሉን አስታውቀዋል።
የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከተሰጣቸው ውስጥ ከ2 ሺህ በላይ የሚሆኑት ወደ ሥራ በመግባት ከ54 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል በከተማዋ ኢኮኖሚ ውስጥ በማንቀሳቀስ ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን ገልጸዋል።
በመንግሥትና በግል አጋርነት በተቀረጹ የተለያዩ የልማት ዘርፎችና ፕሮጀክቶችም፣ በአምስት ዓመታት ውስጥ ከ1.3 ትሪሊዮን ብር በላይ የካፒታል ኢንቨስትመንት በመሳብ እመርታዊ ውጤት መገኘቱን አስታውቀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የሀብት ፍሰትና የልማት መነቃቃት እያስተናገደች መሆኗን የጠቆሙት ከንቲባዋ፤ የግል ባለሀብቱን ተሳትፎ በከፍተኛ ደረጃና ፍጥነት በማሳደግ፣ በርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን አስረድተዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026