የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በክልሉ የከበሩ ማዕድናትን በማልማት የውጭ ምንዛሬ ለማዳን ትኩረት ተደርጓል

Sep 23, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ባህር ዳር ፤ መስከረም 11/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በማዕድን ዘርፍ ተኪ ምርቶችን በማምረት የውጭ ምንዛሬን ለማዳን የሚያስችሉ ተግባራት ተለይተው በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ማዕድን ቢሮ ገለጸ።

የማዕድን ሃብት ልማት በሃገራዊ ኢኮኖሚ ግንባታው ሚናውን እንዲወጣ በመንግስት ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት ዋና ዋና የልማት ዘርፎች አንዱ ሆኖ እየተሰራበት ይገኛል።

በዚህም መሠረት በአማራ ክልል በበጀት ዓመቱ በማዕድን ዘርፍ ተኪ ምርቶችን በማምረት የውጭ ምንዛሬን ለማዳን የሚያስችሉ ተግባራት ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ወደ ሥራ መገባቱም ተገልጿል።


የቢሮው የህዝብና ሚዲያ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዝናው አበበ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የማዕድን ሃብቱን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በጥናትና ምርምር ከመለየት ባለፈ ወደ ልማት በማስገባት ከፍተኛ መሻሻል ተመዝግቧል።

በተለይ የዘርፉ ምሁራንን በማሳተፍ በተካሄደ ሃብቱን የመለየት ጥረትም ወርቅን ጨምሮ ከፍተኛ መጠን ያለው የኮንስትራክሽን ፣ የኢንዱስትሪ፣ የሃይልና መሰል ግብአት የሚውሉ ማዕድናት መገኘታቸው ነው የተገለፀው።

በሃገራዊ ኢኮኖሚ እድገቱ ማበርከት ያለበትን ሚና በመወጣት በኩል ተስፋ ሰጭ ውጤት እየተገኘ መምጣቱን ገልፀዋል።

ውጤቱን ይበልጥ ለማሳደግም በዚህ በጀት ዓመት ከዘርፉ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ በማሳደግና ተኪ ምርቶችን አምርቶ የውጭ ምንዛሬ በማዳን በኩል በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በክልሉ 84 ሺህ 800 ኪሎግራም በላይ ወርቅን ጨምሮ እሴት የተጨመረበት የኦፓል ማዕድን አምርቶ ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከ175 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ጠቅሰዋል።


እንዲሁም ከ7 ነጥብ 9 ሚሊዮን ቶን በላይ የተለያዩ አይነት ተኪ የማዕድን ምርቶችን በሃገር ውስጥ አምርቶ በመጠቀም ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ የማዳን ስራ ይሰራል ነው ያሉት።

ክልሉ እምቅ የሆነ የከበሩ ማዕድናት ባለቤት እንደሆነ አንስተው፤ እቅዱን ለማሳካትም በተደራጀ አግባብ እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

በክልሉ ባለፈው በጀት ዓመት ወደ ውጭ ሃገራት ከተላኩ የከበሩ ማዕድናት ከ18 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ መገኘቱንም አስታውሰዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የእጣንና ሙጫ ደኖችን ለመንከባከብ የማህበረሰብ አቀፍ የደን ጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ ነው

ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...

Sep 20, 2026

በባህር ዳር ከተማ አስተማማኝ ሰላምና ተጨባጭ የልማት ስራዎችን ማከናወን ተችሏል

ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል...

Sep 15, 2026

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026