የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በአስተዳደሩ የሕብረተሰቡን የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች በላቀ ደረጃ የመፍታት ሂደቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል

Sep 24, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ድሬደዋ፤ መስከረም 13/2018 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ አስተዳደር የከተማና የገጠሩን ሕብረተሰብ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች በላቀ ደረጃ የመፍታት ሂደቱ ተጠናክሮ መቀጠሉን የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጁሃር ገለጹ።

የድሬደዋ ከተማን ሁለንተናዊ ልማትና ዕድገት የሚያሳልጥ የ4 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሆነ።

የአስፋልት መንገዱን መርቀው አገልግሎት ያስጀመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር፤ የድሬዳዋ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አብዲ ሙክታር እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ናቸው።

የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር በምረቃው ወቅት እንዳሉት፤ የከተማና የገጠሩን ሕብረተሰብ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች በላቀ ደረጃ የመፍታት ሂደቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በከተማው ወረዳ ዘጠኝ የተገነባው ደረጃውን የጠበቀ የአስፋልት መንገድ ከጅቡቲ የወጪና የገቢ ንግድ ዕቃዎች ከሚመላለሱበት የክፍያ መንገድ ጋር የሚያገናኝ በመሆኑ ጠቀሜታውን የጎላ ያደርገዋል።

የመደመር መንግሥት ምቹ የመኖሪያና የሥራ አካባቢ ለመፍጠር እያከናወናቸው ከሚገኙት ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ዛሬ ተመርቆ ለአገልግሎት የበቃው የዘመናዊ አስፋልት መንገድ መሆኑንም ከንቲባው ተናግረዋል።

ባለፉት አምስት ዓመታት ከ22 ኪሎ ሜትር በላይ የዘመናዊ አስፋልት መንገድ ግንባታ እና ከኮሪደር ልማት ጋር የተሰናሰሉ አዳዲስ የመኪናና የእግረኛ መንገዶች ተገንብተው ለአገልግሎት መብቃታቸውን ገልጸዋል።

በዚህም የመሠረተ ልማት አውታሮችን በማስፋፋትና ለኑሮ ምቹ የሆኑ አካባቢዎችን ከመፍጠር ባለፈ የሕዝቡን ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመፍታት ሂደቱ መጠናከሩን አመልክተዋል።

የድሬዳዋ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ጀማል ኢብራሂም በበኩላቸው፣ የከተማዋ ዳርቻ አካባቢ ነዋሪዎችን የዘመናት የመንገድ ጥያቄ ለመመለስ የተደረገው ዘርፈ ብዙ ርብርብ አዎንታዊ ምላሽ ማግኘቱን ገልጸዋል።

መንገዱ የወረዳው ነዋሪዎችን ብቻ ሳይሆን የከተማዋን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች በላቀ ደረጃ እንደሚያሳድግም ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

መንገዱ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ መንግሥት የዜጎችን ጥያቄዎች ለመፍታት ያሳየውን ቁርጠኝነት የተመለከትንበት ነው ያሉት ደግሞ የወረዳው ነዋሪ ወይዘሮ ፋጡማ አብዲ ናቸው።

አቶ ሰሎሞን አሰፋ የተባሉ ነዋሪ በበኩላቸው፣ መንገዱ በይፋ አገልግሎት መጀመሩ የድሬዳዋ አስተዳደር አመራሮች ለነዋሪው የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የእጣንና ሙጫ ደኖችን ለመንከባከብ የማህበረሰብ አቀፍ የደን ጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ ነው

ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...

Sep 20, 2026

በባህር ዳር ከተማ አስተማማኝ ሰላምና ተጨባጭ የልማት ስራዎችን ማከናወን ተችሏል

ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል...

Sep 15, 2026

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026